History

የኢትዮጵያ ብስክሌት እንቅስቃሴ ሂደት

Blog Image

የብስክሌት ስፖርት ወደ ሀገራችን የገባው ከጣሊያን ወረራ በፊት በአገር ውስጥ ይዘወተር እንደነበር፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሂደት በተለይም ከዛሬ 65 ዓመት በፊት የመጓጓዣ አገልግሎት በብስክሌት ስለነበር የስፖርቱ እንቅስቃሴ ከሌሎች ስፖርቶች ሁሉ የተሻለ ተወዳጅነት እንደነበረው ይነገራል፡፡ ጣሊያን ወደ ሀገራችን ሲመጣ ብዙ የውጪ አገር ተወዳደሪዎች በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ በኤርትራ ስፖርቱን ያዘወትሩ ስለነበረ የብስክሌት ስፖርት በአገር ውስጥ ተወዳጅ የሆነ ከመምጣቱም በላይ የጣሊያን ተወላጅ ለብቻቸው በአዲስ አበባ ከተማ በመርካቶና በጃንሜዳ ዙሪያ ከፍተኛ ውድድሮች ያደርጉ እንደነበርና በተለይም ከ1930 - 1933 ዓ.ም በነበረው ወቅት በኢትዮጵያ ወጣቶች መካከል በሚደረጉት ውድድሮች ከፍተኛ አድናቆት እንደነበር 
በዚሁ የብስክሌት እንቅስቃሴ እድገት በመነሳት በ1944 ዓ.ም. የብስክሌት ፌዴሬሽን በህጋዊነት ተቋቁሞ በመንቀሳቀስ በ1948 ዓ.ም. በሜልቦርን ኦሎምፒክ ብስክልት ለመካፈል ተችሏል

  • 2025-10-09 05:45:34