History

ብስክሌት ወደ አፍሪካ ያስገቡት

Blog Image

ብስክሌት ወደ አፍሪካ ያስገቡት ኮሎኒያሊስቶች እንደሆኑ ይነገራል፣ ይገለገሉበትም የነበረው ለመጓጓዣነት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡ 
ለ1937 በአይቮሪኮስት ሀገር በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የብስክሌት ውድድር ተጀመረ፡፡ የሚመራው በኮሚቴ ብቻ ነበር፣ በአሁኑ ጊዜ ከ40 ያላነሱ አገሮች የብስክሌት ፌዴሬሽን በማቋቋማቸው የአፍሪካ የብስክሌት ኮንፌዴሬሽን ተቋቁሟል፡፡ ሆኖም ግን እንደ አትሌቲክስ፣ እንደ እግር ኳስና እንደ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን የተጠናከረ አልነበረም፡፡ 
የብስክሌት ስፖርት በአፍሪካ እንዳይስፋፋ ከፍተኛ ማነቆ የሆነው ነገር ቢኖር የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ውድቀትና ውድድሮች የሚደረጉት በአራት ዓመት አንድ ጊዜብቻ በመሆናቸው ነው፡፡ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ብስክሌት ኮንፌዴሬሽን ከተቋቋመበት ከ1954 ዓ.ም. ጀምሮ ጠንካራ ኮንፌዴሬሽን ሲሆን የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ከስሩ ያንቀሳቅሳል፡፡ 

  • 2025-10-09 05:42:26